Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአስተዳደር ቢዝነስ ልማትና የአይሲቲ ጉባኤ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገር አቀፍ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአስተዳደር ቢዝነስ ልማትና የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ጉባኤ በድሬዳዋ እየተካሄደ ነው።
የሣይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ባዘጋጀው በዚህ ጉባኤ፥ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በዲጂታል መሠረተ ልማት፣ በመረጃ ደህንነትና በቴክኖሎጂ አጠቃቀም ዙሪያ የተሰሩ ስራዎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
የሳይንስና ከፍተኛ ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ፥ በዩኒቨርሲቲዎች የሀብት ብክነትን ለማስቀረት የዲጂታል መሠረተ ልማቶች የማይተካ ሚና እንደሚጫወቱ ተናግረዋል።
በመሆኑም አመራሩን በዘርፉ ብቁ በማድረግ ወደ ዲጂታል ትራስፎርሜሽን ለመሸጋገር የሚሰሩ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው ብለዋል።
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ዑባህ አደም በበኩላቸው፣ መንግስት በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ዘርፍ የያዘውን ዕቅድ ለማሳካት ዩኒቨርሲቲው ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።
ዩኒቨርሲቲው 195 ሚሊየን ብር ወጪ በማድረግ በግቢው የኢንተርኔት ማስፋፊያና የዳታ ማዕከል ግንባታዎች ማከናወኑንም ለአብነት አንስተዋል።
ለሁለት ቀናት በሚቆየው በዚህ ጉባኤ ከ40 ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተውጣጡ 300 የቢዝነስ ልማት ዳይሬክተሮችና ምሁራን ተሳታፊዎች ናቸው።
በእዮናዳብ አንዱዓለም
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version