አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ አራት ኢትዮጵያውያን ከስኬታማና ተፅዕኖ ፈጣሪ 100 አፍሪካውያን ሴቶች ዝርዝር ውስጥ ተካተቱ።
በዝርዝሩ ውስጥ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅን ጨምሮ የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስትር ፊልሰን አብዱላሂ፣ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ እና የሶል ሬብልስ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ቤተልሄም ጥላሁን ተካተዋል።
ዝርዝሩን ያወጣው አቫንስ ሚዲያ (100women.avancemedia.org ) የተሰኘ ድርጅት ሲሆን፥ በየዓመቱ ስኬታማና ውጤታማ የሆኑ 100 የአፍሪካ ሴቶችን ስም ዝርዝር በማውጣት ይታወቃል።
በድርጅቱ ዝርዝር ለመካተት የአመራርና አፈፃፀም ክህሎት፣ በግል ያስመዘገቡት ስኬት፣ እውቀት ማጋራት እና የማይመቹ አሰራሮችን መቀየር የሚሉት በድርጅቱ ዝርዝር ውስጥ ለመካተት የሚያስችሉ መስፈርቶች መሆናቸውን ከድርጅቱ ድረ ገጽ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!