አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ የጸጥታ ችግር ለመፍጠር በመንቀሳቀስ የተጠረጠሩ 85 ሰዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ፖሊስ አስታወቀ፡፡
የአሶሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ኮማንደር ቡሽራ አልቀሪብ ለኢዜአ እንዳሉት፤ ተጠርጣሪዎቹ የከተማውን የሰላምና ጸጥታ ሁኔታ አስተማማኝ ለማድረግ የተጣለውን የሰዓት እላፊ ገደብ ጥሰው ሲንቀሳቀሱ በመገኘታቸው በቁጥጥር ስር ውለዋል።
ተጠርጣሪዎቹ በሃገር መከላከያ ሠራዊት፣ በፌዴራል ፖሊስ፣ በክልሉ ልዩ ሃይልና በነዋሪዎች የተቀናጀ የጸጥታ አስከባሪ ሃይል አማካኝነት መሆኑን የገለጹት ኮማንደር ቡሽራ፥ ከተጠርጣሪዎቹ መካከል የአሸባሪው ህወሓት ርዝራዦች እንደሚገኙበት ጠቅሰዋል።
ከተጠርጣሪዎቹ መካከል የ53ቱ የባንክ ሂሳብ፣ ተሽከርካሪዎችና ሌሎች ንብረቶች በፍርድ ቤት ትዕዛዝ መታገዱን ተናግረዋል፡፡
ተጠርጣሪዎቹን ለሕግ ለማቅረብ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ኮማንደር ቡሽራ አስታውቀዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!