Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በካፋ ዞን 701 ወጣቶች በሰፈራ ፕሮግራም የስራ እድል ተጠቃሚ መሆናቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በካፋ ዞን ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አቶ በላይ ተሠማ የተመራ ልዑክ በሺሾ እንዴ ወረዳ በሽመሮ እና ሂሪዮ ቀበሌ በውስጥ ሰፈራ ፕሮግራም ስራ ዕድል የተፈጠረላቸው የ701 የወጣቶች ስራ እንቅስቃሴ ጉብኝት አድርጓል፡፡
የወረዳው ህብረተሰብ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነቱ እንዲረጋገጥ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ መልኩ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የወረዳው ዋና አሰተዳዳሪ አቶ አሰረስ አስፋው ተናግረዋል፡፡
በወረዳው በሽመሮ እና ሂሪዮ ቀበሌዎች በውስጥ ሰፈራ ለ701 ስራ አጥ ወጣቶች ስራ ዕድል እንደተፈጠረላቸውም ገልጸዋል።
ወጣቶቹ በቂ ምርት አምርተው ለገበያ እንዲያቀርቡ በወረዳው በኩል የትራክተር ድጋፍ የሚያገኙበት መንገድ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየተሠራ እንደሚገኝም ነው የገለፁት፡፡
ተጠቃሚ ወጣቶቹ በበኩላቸው ከዚህ ቀደም ስራ አጥ ሆነው የቤተሰብ ድጋፍ ሲጠይቁ እንደነበር ገልጸው÷ አሁን ግን የተለያዩ የግብርና ስራዎችን እያከናወኑ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በአካባቢው የሚስተዋለው የመሰረተ ልማት ችግር እንዲፈታላቸው ጠይቀዋል።
የካፋ ዞን ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አቶ በላይ ተሠማ በበኩላቸው በሰፈራ ጣቢያው የስራ ዕድል የተፈጠረላቸው የወጣቶች የስራ እንቅስቃሴ የሚበረታታ መሆኑን ጠቁመው÷ ተሞክሮውን በዞኑ በሁሉም ወረዳዎች የማስፋት ተግባር ይከናወናል ብለዋል።
ወጣቶቹ በተሰጣቸው መሬት ላይ ምርትና ምርታማነታቸው እንዲያድግ የግብዓትና የባለሙያ ድጋፍ እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ ድጋፎች እንደሚደረጉላቸውም አንስተዋል፡፡
የሚስተዋለውን የመሰረተ ልማት ክፍተት ለመቅረፍም ከወረዳው አስተዳደርና ከሚመለከታቸው ባላድርሻ አካላት ጋር ቅንጅት በመፍጠር ጥረት ይደረጋል ማለታቸውን ከደቡብ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያሳያል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
Exit mobile version