የሀገር ውስጥ ዜና

በጎንደር ከአሸባሪው ህወሓት ጋር ግንኙነት ያላቸው 78 ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

By Melaku Gedif

August 31, 2021

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጎንደር ከተማ ከአሸባሪው የህውሓት ቡድን ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸው 78 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑ ተገለጸ፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ፓሊስ መምሪያ ሃላፊ ኮማንደር አየልኝ ታክሎ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷የጁንታው ተላላኪዎች ወደ ከተማዋ ሰርገው በመግባት የሽብር ጥቃት እንዳይፈጽሙ ጠንካራ የኬላ ፍተሻና የጸጥታ ስራ እየተከናወነ ነው፡፡