Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በደቡብ ወሎ ከ200 በላይ ሰርጎ ገቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ200 በላይ ሰርጎ ገቦችን በቁጥጥር ስር በማዋል ተጨማሪ የማጣራት ስራ እየሠራ መሆኑን የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር ገለፀ።
የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሰይፍ ሰይድ ከጣቢያችን ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደተናገሩት፥ ተጠርጣሪ ሰርጎ ገቦቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በፀጥታ መዋቅሩ እና በማህበረሰቡ የተቀናጀ ጥረት ነው ብለዋል።
ዞኑን ከሰርጎ ገቦች እና ከሚያስከትሉት ሁለንተናዊ ችግር ለመከላከል የተፈጠሩ አደረጃጀቶችን ወደ ማህበረሰቡ በማውረድ የአካባቢ ጥበቃ ስራው የተጠናከረ እንዲሆን እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።
የጁንታውን የበሬ ወለደ ወሬ ከመስማት በመራቅ ማህበረሰቡ አካባቢውን በመጠበቅ የተበታተነውን የጠላት ኃይል ለመጠራረግ የሚደረገውን ዘመቻ በቻለው ሁሉ እንዲያግዝም ጥሪ ቀርቧል።
በእሸቱ ወ/ሚካኤል
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version