Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ጠ/ሚ ዐቢይ ከጂቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ዑመር ጊሌ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከጂቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ዑመር ጊሌ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ በስልክ ተወያዩ።
በውይይታቸውም የሁለቱን ሃገራት ታሪካዊ ግንኙነት በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
መሪዎቹ በቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር ያደረጉ ሲሆን÷የጋራ ተጠቃሚነትን ባከበረ መልኩ የሁለትዮሽና የቀጠናዊ ግንኙነትን ለማጠናከር መነጋገራቸውም ታውቋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version