Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፍ ያስተማራቸውን ተማሪዎች አስመረቀ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 23፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ በመካነ ሰላም ግቢ በተለያዩ የትምህርት ዘርፍ ያስተማራቸውን 774 ተማሪዎች አስመረቀ፡፡

ከተመራቂዎቹ ውስጥ 320 ያህሉ ሴቶች ናቸው ተብሏል፡፡

የአራተኛው ትውልድ ከሚባሉት 11 ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ እንደሆነ የሚጠቀሰው መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ለሁለተኛ ጊዜ ነው ተማሪዎቹን ያስመረቀው፡፡

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ዴኤታ እና የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር መስፍን አሰፋን ጨምሮ የፌዴራል፣ የክልል እና የዞን የክብር እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

በተመሳሳይ የወላይታ ሶዶ ዩንቨርስቲ የዳውሮ ታርጫ ግቢ በተለያየ የትምህርት ክፍል በቀን በመደበኛና በሳምንት መጨረሻ መርሀግብር ለ4ኛ ዙር ያስተማራቸውን ተማሪዎች አስመርቋል።

የዩንቨርስቲ ግቢው 32 የዳውርኛ ቋንቋ ተመራቂ ተማሪዎችን ጨምሮ በተለያየ የትምህርት ክፍል የተማሩ በርካታ ተማሪዎችን ነው ያስመረቀው።

በምርቃ መርሀግብሩ የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ፕሮፈሰር ታከለ ታደሰ፣ የዳውሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ተክሌ በዛብህ፣ የተመራቂ ተማሪዎች ቤተሰቦችና ለሎች በርካታ እንግዶች መገኘታቸውን ከየዩኒቨርሲቲዎቹ ያኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version