የሀገር ውስጥ ዜና

በጋምቤላ ክልል “እኔም ለሀገሬ ወታደር ነኝ” በሚል መሪ ቃል የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ የእግር ጉዞ ተካሄደ

By Feven Bishaw

August 29, 2021

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 23፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል “እኔም ለሀገሬ ወታደር ነኝ”፤ “ኢትዮጵያን ለማዳን እዘምታለሁ”በሚል መሪ ቃል የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ የእግር ጉዞ ተካሂዷል፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ቴንኩዌይ ጆክ፣ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ላክዴር ላክባክ፣ የክልሉ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ታይዶር ቻምባንግን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮችና የከተማው ማህበረሰብ መሳተፉን ከጋምቤላ ክልል ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።