Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አሸባሪው ህወሓት በፈጸመው ግፍ በንፋስ መውጫ ከ25 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች ለእለት ምግብ እጥረት ተጋልጠዋል

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 23፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ልማት ማህበር ከ1 ሚሊየን ብር በላይ ወጭ የተደረገበት 220 ኩንታል የስንዴ ዱቄት በንፋስ መውጫ ለተጎዱ ነዋሪዎች ድጋፍ አድርጓል።

የማህበሩ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አራጋው ታደሰ ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት እንዳሉት የህወሓት አሸባሪ ቡድን የንፋስ መውጫ ከተማን ተቆጣጥሮ በነበረበት ወቅት ንጹሃን ዜጎችን በመግደል፣ ሃብትና ንብረት በመዝረፍና በማውደም ህብረተሰቡ ለእለት ምግብ እጦት እንዲጋለጥ አድርጓል።

ማህበሩ ከ1 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጭ የገዛውን 220 ኩንታል የስንዴ ዱቄት በከተማው ለችግር ለተጋለጡ
የነፋስ መውጫ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ አለምነው ክንዴ በበኩላቸው ቡድኑ በፈጸመው ግፍ ከ8 ሺህ 500 በላይ የቤተሰብ አባላት የሆኑ ከ25 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች ለእለት ምግብ እጥረት መጋለጣቸውን ጠቅሰዋል።

የአማራ ልማት ማህበር ለወገኖቹ ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

ድጋፉ ለተጎዱ ነዋሪዎች በፍትሃዊነት እንደሚከፋፈል ጠቁመው ሌሎች ረጅ ድርጅቶችም ድጋፍ እንዲያደርጉ መጠየቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version