Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አሸባሪው ሸኔ ሚናውን የለየ ሽብርተኛ ስለመሆኑ ህዝቡ በግልጽ እየተረዳ ነው

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 23፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ሸኔ ሚናውን የለየ ሽብርተኛ ስለመሆኑ ህዝቡ በግልጽ እየተረዳ መምጣቱን የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄነራል አራርሳ መርዳሳ አስታወቁ፡፡

ኮሚሽነር ጄነራል አራርሳ፤ሽብርተኞቹ ሸኔና ትህነግ ከዚህ በፊት ግንኙነት የነበራቸው ቢሆኑም ሲካካዱ የነበሩ ናቸው ብለዋል።

አሁን በአንድነት ለመሥራት የደረሱበት ስምምነት እውነታውን አደባባይ ያወጣ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

አሸባሪውን ሸኔ የፈጠረው ራሱ አሸባሪው ትህነግ ያሉት ኮሚሽነር ጄነራል አራርሳ መርዳሳ ትህነግ ሸኔን በመጠቀም የኦሮሞን ህዝብ፤ መልሶም ሸኔን ሲያጠቃ መቆየቱን አስታውቀዋል፡፡

አሸባሪው ሸኔ ከትህነግ ምንም ልዩነት እንደሌለውና ቅጥረኛ እንደሆነ፤ በብሄር፣ በዴሞክራሲና በነፃነት ስም ይዞት የተነሳው ጥያቄ ተረት ተረት መሆኑን ህዝቡ አሁን በአግባቡ ተረድቶታል ብለዋል፡፡

አሁን ደግሞ በአደባባይ ሁለቱም አሸባሪ ቡድኖች አንድ መሆናቸውን እና መንግሥትን በጋራ ሆነው ለመጣል መስማማታቸው ማንነታቸውን በግልጽ አመላክቷል ያሉት ኮሚሽነር ጄነራል አራርሳ፤ ይህ እኩይ ዓላማቸው እንዳይሰምር በሁለቱም ላይ እርምጃ እየተወሰደ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

በሰሜኑ ያለው ሽብርተኛው ትህነግ በተወሰደበት ከፍተኛ እርምጃ እብሪቱ እየተነፈሰ እንዳለ ሁሉ በኦሮሚያ ክልል ያደፈጠውም ሸኔ እየተመታ ነው ማለታቸውን ኢፕድ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version