Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

”ኑ ኢትዮጵያን እናልብሳት” የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 23፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ”ኑ ኢትዮጵያን እናልብሳት” የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች፣ አትሌቶችና ታዋቂ ግለሰቦች በተገኙበት በቢሾፍቱ ከተማ ተካሄደ።

መርሃ ግብሩ በግብርና ሚኒስቴር፣ በአካባቢ ደንና አየር ንብረት ኮሚሽን፣ በተፋሰሶች ልማት ባለስልጣን፣ በቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር፣ በትራንስፎርሜሽናል ሙዚቃና ማስታወቂያ ድርጅት እና በምዕራፋ ፕሮዳክሽን አዘጋጅነት የተካሄደ ነው፡፡

የቢሾፋቱ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አለምፀኃይ ሽፈራው፤ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና ትብብር የብልጽግና ከፍታዋን እንድትላበስ ማድረግ ከሁሉም ይጠበቃል ያሉ ሲሆን÷ የአረንጓዴ አሻራቸውን ለማሳረፍ ለመጡትም ምስጋና አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ፕሬዚደንት ኮሎኔል ደራርቱ ቱሉ በኢትዮጵያን እናልብስ የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ ላይ በመገኘት አሻራዋን በማኖሯ ደስተኛ መሆኗን ገልፃለች።

አረንጓዴ አሻራ ሲታሰብ የአየር ንብረት ለውጥ ይታሰባል፤ በመሆኑም የአካባቢ ደህንነትን መጠበቅ ለነገ ትውልድ የተሻለች ኢትዮጵያን ለማስረከብ ይገባል ብላለች።

በመርሃ ግብሩ ላይ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች፣ አትሌቶች እና ታዋቂ ግለሰቦች ተገኝተው ለኢትዮጵያ አረንጓደዴ አሻራቸውን ማሳረፋቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version