አዲስ አበባ ፣ ጥር 23 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኤርትራን ጨምሮ ለስድስት ሃገራት ዜጎች የሚሰጠውን የስደት ቪዛ አገዱ።
እገዳው ኤርትራ፣ ናይጀሪያ፣ ታንዛኒያ፣ ሱዳን ኪርጊዝታን እና ማይንማር ዜጎች ላይ የተጣለ ነው።
አዲሱ መመሪያ የሃገራቱ ዜጎች አሜሪካ የምትሰጠውን የስደት ቪዛ እንዳያገኙ የሚከለክል ሲሆን፥ የጎብኝ ቪዛ ግን ይፈቅድላቸዋል።
ይህን ተከትሎም የናይጄሪያ፣ ኤርትራ፣ ኪርጊዝታን እና ማይንማር ዜጎች ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ቪዛ አይሰጣቸውም።
የታንዛኒያ እና የሱዳን ዜጎች ደግሞ የዲቪ ሎተሪ ተጠቃሚ አይሆኑም።
የአሁኑ እገዳ ሃገራቱ የአሜሪካን የጸጥታ ሕግና የመረጃ መጋራት ደረጃ ማሟላት አልቻሉም በሚል የተጣለ ነው ተብሏል።
ምንጭ፦ ቢቢሲ