Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮ ቴሌኮም 80 ሚሊዮን ደንበኞችን ማስተናገድ የሚችል የቀጣይ ትውልድ ቢዝነስ ሳፖርት ሲስተም ተግባራዊ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ-ቴሌኮም 80 ሚሊዮን ደንበኞችን ማስተናገድ የሚችል አቅም የፈጠረ የቀጣይ ትውልድ ቢዝነስ ሳፖርት ሲስተም (NGBSS) ተግባራዊ አድርጓል።

አዲሱን ቴክኖሎጂ በተመለከተ የተዘጋጀ መርሃ ግብሩ ላይ ገለፃ ያደረጉት የኢትዮ-ቴሌኮም የመረጃ ዋና ኃላፊ አቶ እንዳለ አስራት÷ “አሰራሩ የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢውን በቀላሉ ከደንበኛው ጋር የሚያገናኝ ነው” ብለዋል።

የመሰረተ ልማት ችግር፣ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ማስፈለጉ፣ የአገልግሎት ጥራት እየቀነሰ መሄድ፣ ኩባንያው ወደ ውድድር እየገባ መሆኑ ኢትዮቴሌኮም ቴክኖሎጂውን ተግባራዊ እንዲያደርግ እንዳስቻለው ጠቁመዋል።

የኢትዮቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ÷ ቴክኖሎጂው በራስ አቅም እንደተሰራ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ኢትዮቴሌኮም ቀዳሚና ተመራጭ አገልግሎት ሰጭ ሆኖ ለመጓዝ በሚያደርገው ጥረት የቴክኖሎጅው መጀመር ድርሻው የጎላ እንደሆነ ጠቅሰው÷ በስራው ላይ የተሳተፉ ባለሙያዎችን አመስግነዋል።

“ስራው በቅንጅትና በጥሩ አመራር ተግባራዊ መሆኑ ጀምረን መጨረስ እንደሚቻል ያሳየ ነው” ብለዋል።

የኩባንያውን አገልግሎት አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን የሚያስችለው ቴክኖሎጂ በየደረጃው ፍተሻዎች ከተደረጉለት በኋላ ብቁ መሆኑ በመረጋገጡ ወደ ስራ እንደገባ ተናግረዋል።

“የቴክኖሎጂው ፕሮጀክት 43 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የጠየቀ ነው” ብለዋል ዋና ስራ አስፈጻሚዋ።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version