Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኤቨርተንና ሌስተር ሲቲ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ዛሬ 11 ሰዓት ላይ በተደረጉ አምስት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ሁለቱ በመሸናነፍ ሲጠናቀቁ ሶስቱ ደግሞ በአቻ ውጤት ተጠናቀዋል፡፡

በዚህም መሰረት ኤቨርተንና ሌስተር ሲቲ ተጋጣሚዎቻቸውን ሲያሸንፉ÷ አስቶንቪላ ከብሬንት ፎርድ፣ ኒውካስል ዩናትድ ከሳውዝ ሃምፕተን፣ ዌስትሃም ዩናትድ ከክሪስታል ፓላስ አቻ ተለያይተዋል፡፡

ኤቨርተን ብራይተንን 2ለ0 ሲያሸንፍ፣ ሌስተር ሲቲ ደግሞ ኖርዊች ሲቲን 2ለ1 በሆነ ውጤት ረቷል፡፡

አስቶንቪላ ከብሬንት ፎርድ አንድ አቻ፣ ኒውካስትል ዩናይትድና ሳውዝ ሃምፕተን ሁለት እኩል እንዲሁም ዌስትሃም ዩናይትድና ክሪስታል ፓላስም ሁለት አቻ በሆነ ውጤት ጨዋታቸውን አጠናቀዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version