Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የእግር ኳስ ክለቦች ለጀግናው መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ለማድረግ ወሰኑ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ የእግር ኳስ ክለቦች ለጀግናው መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ለማድረግ ወስነዋል፡፡

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር ጠቅላላ ጉባዔ ወደፊት ክለቦች ከብሮድካስቲግ ገቢ ከሚያገኙት ድርሻ ታሳቢ የሚሆን 500 ሺህ ብር እያንዳንዳቸው ተቀናሽ በማድረግ ነው ድጋፍ ለማድረግ የወሰኑት፡፡

በዚህም 16ቱም ክለቦች በጋራ 8 ሚሊየን ብር ገቢ ለማድረግ መስማማታቸውን ከእግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version