የሀገር ውስጥ ዜና

የአማራና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የጋራ የልማት፣ የሰላምና የትብብር ስምምነት መድረክ እየተካሄደ ነው

By Meseret Awoke

August 28, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22፣ 2023(ኤፍ ቢ ሲ) የአማራና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎችን መልካም ጉርብትና የበለጠ የሚያጠናክር የጋራ የልማት፣ የሰላምና የትብብር ስምምነት መድረክ በባህርዳር ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ የሁለቱን ክልሎች ልማት ማፋጠንና ዘላቂ ሰላምን ማረጋገጥ ላይ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ተብሏል ።

በምክክር መድረኩ በሁለቱ ክልሎች የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊና የሰላም ስምምነት እንደሚካሄድ ኢቢሲ ዘግቧል።

ሌተናል ጄኔራል አስራት ዴኔሮ ስምምነቱ ከዚህ ቀደም ይከሰቱ የነበሩ መፈናቀልና ሞትን ለማስቆም አይነተኛ ሚና አለው ብለዋል።

በመድረኩ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር፣ የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሃሰን፣ የመተከል የተቀናጀ ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ ሌተናል ጄኔራል አስራት ዴኔሮ እንዲሁም የሁለቱ ክልሎች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!