የሀገር ውስጥ ዜና

በቤንች ሸኮ ዞን አሸባሪው ህወሓትን የሚያወግዝ ሰልፍ ተካሄደ

By Meseret Awoke

August 28, 2021

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤንች ሸኮ ዞን አሸባሪው ህወሓትን የሚያወግዝ እና ለመከላከያ ሰራዊት የድጋፍ ሠልፍ ተካሄደ፡፡

አሸባሪዉ ህወሃት በሀገራችን ላይ የከፈተውን ጦርነት ለመመከት የዞኑ ወጣቶች በአካል ከመዝመት ጀምሮ በገንዘብ ፣በሞራል እና በደም ልገሳ ከፍተኛ አስተዋፆ አበርክተዋል።

በዛሬው ዕለትም ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ያላቸውን አጋርነት በድጋፍ ሠልፍ ገልፀዋል።

በሀገር ህልውና ላይ ትልቅ ስጋት የደቀነዉ ፅንፈኛ ቡድን ከኢትዮጵያ ምድር ተነቅሎ እስኪጠፋ ለሠራዊቱ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ በሚዛን አማን ከተማ በተደረገው በዚህ ሰልፍ ላይ የተሳተፉ ወጣቶች ገልጸዋል።

ስለ ህወሃት ክፋት ተነግሮን ሳይሆን መከራውን ቀምሰን ያየነው ነው፣ሃገራችን ኢትዮጵያ በኛ ዘመን በጠላቶቿ እጅ አትወድቅም የሚሉና ሌሎችም መፈክሮች በሰልፉ ላይ ተስተጋብተዋል።

ድጋፍ ሰልፉን ምክንያት በማድረግ የደም ልገሳ መርሐ ግብርም ተካሂዷል።

በዘላለም ግዴለው

ተጨማሪ ፎቶ፡- ከደሬቴድ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!