የሀገር ውስጥ ዜና

አሸባሪው ህወሓት ዳሎልን ለመቆጣጠር ያደረገው ሙከራ በአፋር ልዩ ሀይል እና ሚሊሻ ከሸፈ

By Tibebu Kebede

August 28, 2021

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት በአፋር ክልል ዳሎልን ለመቆጣጠር ያደረገው ሙከራ በአፋር ክልል ልዩ ሀይል እና ሚሊሻ ከሽፏል፡፡

ህወሓት በክለሉ በበርሃሌ ወረዳ በርካቶችን ገድሏል፣ አቁሱሏል፣ ከቤት ንብረታቸውም አፈናቅሏል እንዲሁም ቅርሶችን አውድሟል፡፡

ቡድኑ በከባድ መሳሪያ ጥቃት ቢፈጽምም የአፋር ልዩ ሃይል አባላት ባላቸው አነስተኛ መሳሪያ በማጥቃት ትልቅ ጀብድ እንደፈጸሙ የዞን 3 ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ አሊ በስፍራው ለሚገኘው ባልደረባቸን ነግረውታል፡፡

አሁን ላይም ልዩ ሃይሉ ከፍተኛ ድል እያስመዘገበ ነው ብለዋል ዋና አስተዳዳሪው፡፡

በአሸባሪው ቡድን ከቀያቸው የተፈናቀሉ ከ6 ሺህ በላይ ዜጎች ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑን የገለጹት አቶ መሀመድ፥ ድጋፉ በቂ ባለመሆኑ ትኩረት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።

በጌታሰው የሺዋስ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!