የሀገር ውስጥ ዜና

የኬንያ የቱሪዝም ባለሙያዎች በኢትዮጵያ ጉብኝት እያደረጉ ነው

By Alemayehu Geremew

August 28, 2021

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 22፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከኬኒያ የመጡ የቱሪዝም ባለሙያዎች በኢትዮጵያ ጉብኝት እያደረጉ መሆኑ ተገለፀ።

ቱሪዝም ኢትዮጵያ ያዘጋጀው ይህ ጉብኝት መነሻው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም ሲሆን መዳረሻው ደግሞ ሀረር እንደሆነ ተጠቁሟል።

 

 

 

 

 

 

ጎብኚዎቹ በቆይታቸው አንድነት ፓርክን፣ እንጦጦ ፓርክን፣ አፍሪካ ህብረትንና ድሬዳዋን እንደሚጎበኙ ተጠቁሟል፡፡

የኮሮና ቫይረስ እንደ ሌሎች የዓለማችን ሀገራት ሁሉ በኢትዮጵያ ቱሪዝም ላይም ከፍተኛ ጉዳት እንዳደረሰ የገለጹት የቱሪዝም ኢትዮጵያ ስራ አስፈጻሚ አቶ ስለሺ ግርማ÷ አሁን ላይ አስፈላጊውን የጥንቃቄ መስፈርቶች በሟሟላትና ሙሉ ዝግጅት በማድረግ ጎቢኚዎችን ለመቀበል ተዘጋጅተናል ብለዋል።

በተጨማሪም ቢሮው አዲስ ኮሚሽን በማዋቀር ኢትዮጵያን የጎብኚዎች መዳረሻ ለማድረግ በቁርጠኝነት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

የተጀመረው ስራ ኢትዮጵያን ብቻ የጎብኚዎች መዳረሻ የሚያደርግ ሳይሆን ምስራቅ አፍሪካንም የበለጠ የሚያስተዋውቅ መሆኑን ተናግረዋል።

 

ከኬኒያ የመጡት የቱሪዝም ባለሙያ ጎብኚዎች በበኩላቸው የኢትዮጵያን የመስህብ ስፍራዎች እንደሚያስተዋውቁ ቃል ገብተዋል።