Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 54 ተማሪዎች አስመረቀ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመደበኛና ማታ መርሀ ግብሮች ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 54 ተማሪዎች በዛሬው ዕለት በመጀመሪያ ዲግሪ አስመርቋል።

ዩኒቨርሲቲው በ3ኛ ዙር ካስመረቃቸው ተማሪዎች ውስጥ 428 ተማሪዎች ሴቶች ናቸው።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ገናነው ጎፌ ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ለትምህርት ጥራት ሰጥቶ ብቃትና ክህሎት ያላቸው ተማሪዎችን በማፍራት ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል ።

ዩኒቨርሲቲው ትምህርት የሚሰጥባቸውን ፕሮግራሞች 34 ማድረሱንም ገልጸዋል።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ በበኩላቸው መንግስት ለከፍተኛ ትምህርት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል ።

ተመራቂ ተማሪዎች ሀገራቸው ከችግር ተላቃ በእድገት ጎዳና እንድትራመድ በማድረግ የቀሰሙትን እውቀትና ልምድ ወደ ተግባር ሊቀይሩ ይገባል ብለዋል።

ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በሀገሪቱ የሚታዩ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ብልጽግና እንዲመጣ ከፍተኛ ሃላፊነት መወጣት አለባቸው ማለታቸውን ኢብኮ ዘግቧል።

ማህበራዊ ትስስር እንዲላላ ባለፋት 27 አመታት መሰራቱን የገለጹት ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ ህብረብሔራዊ አንድነት እንዲመጣ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ትልቅ ሚና ይጠበቅባቸዋልም ነው ያሉት።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version