የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ በአዋሬ አካባቢ ያሳደሱትን የአቅመ ደካማ መኖሪያ ቤት አስረከቡ

By Tibebu Kebede

August 28, 2021

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአዋሬ አካባቢ ያሳደሱትን የአቅመ ደካማ መኖሪያ ቤት በዛሬው እለት አስረከቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአምስት ሳምንታት በፊት ዓመታዊውን የቤት እድሳት መርኃ ግብር ማስጀመራቸው ይታወሳል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ ሁሉም ዜጎች ለአቅመ ደካማ ማህበረሰቦች እፎይታ ለመስጠት በሚደረጉ ጥረቶች እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!