Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የውጪ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ የሚያበረታቱ የፖሊሲ ማሻሻያዎች ተደርገዋል-ጠ/ሚ ዐቢይ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጪ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ የሚያበረታቱ የተለያዩ የፖሊሲ ማሻሻያዎች መደረጋቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ፡፡

የቡድን 20“ኮምፓክት ዊዝ አፍሪካ ኢኒሼቲቭ” ጉባኤ በዛሬው ዕለት በጀርመኗ መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ሰብሳቢነት በበይነ መረብ ተካሂዷል፡፡

በውይይቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የተለየዩ የአፍሪካ መሪዎች ተሳትፈዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በጉባኤው ላይ ባደረጉት ንግግር÷ የ“ኮምፓክት ዊዝ አፍሪካ ኢኒሼቲቭ” በአፍሪካ ሀገራት ተጨባጭ ለውጥ እንደሚያመጣ እምነታቸው መሆኑን ገልጸዋል፡

ኢትዮጵያ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ በማድረግ የውጪ የእዳ ጫና መቀነስ መቻሏንም አብራርተዋል፡፡

የሀገር ውስጥ ስራ ፈጠራን ለማበረታታትም የተለያዩ ስራዎች መከናወናቸውን ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገለጹት፡፡

የውጪ ሀገር ባለሃብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን ኢንዲያፈሱም በዘርፉ የተለያዩ የፖሊሲ ማሻሻያዎች መደረጋቸውን ጠቅሰዋል፡፡

ለአብነትም የቴሌኮም ዘርፉ በከፊል ለግል ባለሃብቶች እንዲዛወር መደረጉን አንስተዋል፡፡

የኮቪድ-19ኝ ጫናን በመቋቋም የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ ተችሏል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ 4 ቢሊየን ዶላር የሚጠጋ የውጭ ምንዛሬ መገኘቱን ገልጸዋል፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version