Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ተመራማሪዎች የኮቪድ 19 ቫይረስን በ 90 ደቂቃዎች የሚለይ ማስክ መስራታቸውን አስታወቁ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የማሳቹሴትስ ቴክኖሎጂ ኢኒስቲቲዩት እና የሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የጥናት ቡድኖች በጋራ የኮሮና ቫይረስን በትንፋሽ መለየት የሚያስችል ማስክ መስራታቸውን አስታወቁ።

እንደ አጥኚዎቹ ቫይረሱ የሚለየው በማስኩ ውስጥ በሚቀመጡ ቅንጣት መለያዎች አማካኝነት ነው ተብሏል።

ተጠቃሚው ማስኩን አድርጎ ለዚሁ ተግባር አብሮ የተሰራውን ቁልፍ መጫን እንደሚጠበቅበትና ማስኩ ውስጥ አብሮ የተቀመጠው ውሃ እንዲወጣ ማድረግ እንዳለበትም ነው ተመራማሪዎቹ የገለጹት፡፡

ውጤቱን በ 90 ደቂቃ ውስጥ መመልከት እንደሚቻልና የተጠቃሚውን ሚስጥር ለመጠበቅ ሲባል የሚታየው በማስኩ የውስጠኛው ክፍል መሆኑም ነው የተጠቆመው፡፡

አጥኚዎቹ ግኝታቸውን ከጥጥ፣ ፖሊስተር፣ ሱፍ እና ሀር በተሰሩ ማስኮች ላይ በማካተት የተሻለ ውጤት የሚያገኙበትን ስልት እየፈለጉ መሆናቸውንም ገልጸዋል።

በፈረንጆቹ በ2010 አጋማሽ ተመሳሳይ የኢቦላንና የዚካ ቫይረሶችን መለየት የሚያስችል ሞዴል በማሳቹሴት ቴክኖሎጂ ኢኒስቲቲዩት ኢንጅነሪንግ ፕሮፌሰር ጀምስ ኮሊንስ መሰራቱን አር ቲ በዘገባው አስታውሷል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version