Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ቴክኖሎጂን ለማሳደግ የሚዘጋጁ ዓለምአቀፍ የምርምር ጉባኤዎች ፋይዳቸው የላቀ ነው-ዶ/ር አብረሃም

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሳይንስ ምርምርና ቴክኖሎጂን ለማሳደግ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚዘጋጁ ዓለምአቀፍ የምርምር ጉባኤዎች ፋይዳቸው የላቀ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይ ገለጹ።
 
ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት እየተካሄ ባለው 9ኛው ዓለም አቀፍ የተሻሻለ የሳይንስና የቴክኖሎጂ ጉባኤ ላይ በተገኙበት ወቅት ነው።
 
የሀገሪቱን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ለማሳደግ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እያደረጉት ያለው ጥረት በምርምርና በጥናት በታገዘ መልኩ እየተካሄደ መሆኑን አውስተዋል።
 
ዓለምአቀፍ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ጉባኤዎች በዩኒቨርሲቲዎች መካሄዱ ዓለምአቀፍ ተሞክሮዎችን ለማግ፣ት ሁነኛ አማራጭ መሆኑን ነው ሚኒስትሩ የተናገሩት፡፡
 
የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ፍሬው ተገኝ በበኩላቸው÷ ዩኒቨርሲቲያቸው ግንባር ቀደም የምርምር ተቋም እንዲሆን እየተሰራ መሆኑን አመላክተዋል።
 
በተለይ ፓሊ ቴክኒክ ኢንስቲቲዩት የሚገኙ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ በበርካታ የተቋሙ ምሁራን የምርምር ስራዎችን እየሰሩ ነው ብለዋል።
 
ከአሁን ቀደም በነበሩ ዓመታት የተካሄዱ ዓለም አቀፍ ስምንት ጉባኤዎች ስኬታማ ነበሩ ያሉት ዶክተር ፍሬው÷ ዛሬ መካሄድ የጀመረው ዘጠነኛው ጉባኤም ከዚህ የተሻለ እንደሚሆን እንደሚጠበቅ ገልጸዋል።
 
ለሶስት ቀናት በሚቆየው በዚህ ዓለምአቀፍ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ጉባኤ 100 የምርምር ስራዎች በምሁራን ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።
 
በምናለ አየነው
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version