የሀገር ውስጥ ዜና

በታንዛኒያ በእስር ላይ የነበሩ 100 ኢትዮጵያውያን ወደ ሃገራቸው ተመለሱ

By Tibebu Kebede

August 27, 2021

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ታንዛኒያን አቋርጦ ወደ ደቡብ አፍሪካ በሚደረግ ህገ-ወጥ ጉዞ በርካታ ኢትዮጵያውያን በታንዛኒያ መንግስት ቁጥጥር ስር እየዋሉ ለእስር እንደሚዳረጉ ይታወቃል።

ከእነዚህም መካከል 100 ኢትዮጵያውያን አቶ አለማየሁ ከተማ በተባሉ ኢትዮጵያዊ እና ኢንጂነር ጃቢር በተባሉ ታንዛኒያውያ በጎ ፍቃደኛ ግለሰቦች ሙሉ ወጪ ተሸፍኖላቸው ወደ ሃገራቸው ተመልሰዋል።

በርካታ ኢትዮጵያውያን በህገ ወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች በመታለል ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ከፍለው እጅግ አደገኛ የሆነ ህገ ወጥ ጉዞ ያደርጋሉ።

በዚህም በመንገዳቸው ላይ ለርሃብ፣ ለእስር፣ ለስቃይ ብሎም ለሞት እንደሚዳረጉ በታንዛኒያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!