የሀገር ውስጥ ዜና

በህገ ወጥ መንገድ ተከማችቶ የተገኘው ብረት ለገበያ እንዲቀርብ ተወሰነ

By Meseret Demissu

August 27, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ ቦታዎች በህገ ወጥ መንገድ ተከማችቶ የተገኘ ብረት በህጋዊ መንገድ ወደ ገበያ ገብቶ እንዲሸጥና ለመንግስት ገቢ እንዲሆን ተወሰኗል፡፡

በ13 የተለያዩ ቦታዎች በህገ-ወጥ መንገድ ተከማችቶ የተገኘውና በዋጋ አረጋጊ ግብረ-ሀይል በቁጥጥር ስር የዋለው ከ1ሺህ በላይ መኪና ብረት በህጋዊ የግብይት ስርዓቱ ውስጥ ገብቶ እንዲሸጥና ገቢው ለመንግስት እንዲገባ ውሳኔ  መተላለፉን ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር  ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!