Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሀገር የገጠማትን የህልውና አደጋ ለመመከት ሁሉም በጋራ መነሳት እንዳለበት ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገር የገጠማትን የህልውና አደጋ ለመመከት ሁሉም በጋራ መነሳት እንዳለበት የወሎ ግንባር ቃል አቀባይ አቶ ወንዳለ ሀብታሙ ተናገሩ።
የባህርዳር ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ለደሴ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለተፈናቃዮች የተለያዮ ድጋፍ አድርጓል።
በዚህ ወቅትም ቃል አቀባዩ ሁሉም በየዘርፉ ድጋፍ በማድረግ ከገጠመን ችግር በፍጥነት እንድንወጣ በጋራ ሊሰራ ይገባል ብለዋል።
የባህርዳር ጨርቃጨርቅ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂር መንግስቱ አረጋ ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት እንደገለፁት ሀገር ከገባችበት አጣብቂኝ ለማውጣት ሁሉም ሊረዳዳና ሊደጋገፍ እንደሚገባ ገልጸዋል።
ኢንጂነር መንግስቱ 1 ሺህ 500 ፒጃማ ቱታ ከ1 ሺህ በላይ አንሶላ ከ300 በላይ ትራስ በአጠቃለይ 993 ሺህ ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አበርክተዋል።
በቀጣይም አጠቃለይ የጨርቃጨርቅ ፋብሪካዎች በተቀናጀ መንገድ የተሻለ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልፀው በአሁኑ ሰአትም ለመከላከያ ሰራዊት ፣ለልዩ ሀይልና ሚሊሻው የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
ድጋፉን የተረከቡት የደሴ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ሰይድ የሱፍ እየተደረገ ያለው ድጋፍ ሀገሪቱና ወገኖቻችን የተጋረጠባቸውን ፈተና ለመሻገር የሚያግዝ በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባው ጠቁመዋል።
በሀብታሙ ተክለ ስላሴ፣ በመሀመድ አሊና በከድር መሀመድ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version