Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ህብረተሰቡ ራሱን ከኮሮና ቫይረስ እንዲጠብቅ የአማራ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት አሳሰበ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ህዝቡ አሸባሪውን የህወሓት ቡድን ድባቅ ለመምታት የሚያደርገው ተጋድሎ ዓለም አቀፍ ስጋት የሆነውን ኮቪድ19 ወረርሽኝ በመከላከልና በመቆጣጠር ሊደግመው እንደሚገባ የኢንስቲቲዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ በላይ በዛብህ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፓሬት ገልጸዋል።

በኮሮና ቫይረስ የሚያዘው ሰው ቁጥር መጨመር ከፍተኛ ጥንቃቄን የሚጠይቅ እንጂ በመዘናጋት ውስጥ ዋጋ የምንከፍልበት ሊሆን አይገባምም ብለዋል።

አያይዘውም አካላዊ ርቀትን በመጠበቅ ማስክ በመጠቀምና ሌሎች የኮሮና መከላከል መመሪያዎችን በማክበር ህብረተሰቡ መንቀሳቀስ ይገባዋል ነው ያሉት።

ህብረተሰቡ አዲስ ተሻሽሎ የወጣውን መመሪያ ሙሉ በሙሉ እንዲተገብረው ኢንስቲቲዩት እየሰራ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በአንድ ቦታ በብዛት መንቀሳቀስ ዋጋ ስለሚያስከፍል መመሪያው መከበር አለበት ብሏል።

ቀደም ሲል ማህበረሰቡ ለኮሮና መከላከል ይሰጠው የነበረውን ትኩረት አሁን የቫይረሱ ስርጭት እየጨመረ በመሆኑ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግም ጠይቋል።

በምናለ አየነው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version