Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሸኔ በአሸባሪው ህወሃት ቡድን የጦር መሳሪያ እና የገንዝብ ድጋፍ እየተደረገለት የቆየ ሌላኛው የጥፋት እጅ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ሸኔ በአሸባሪው ህወሃት ቡድን የጦር መሳሪያ እና የገንዝብ ድጋፍ እየተደረገለት የቆየ ሌላኛው ህወሃት የጥፋት እጅ መሆኑን ምሁራን ገለጹ።

ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የማህበረስብ ሳይንስ መምህር አና የፖለቲካ ጉዳዮች ተንታኙ ነጋቱ አበበ÷ ሸኔ ለሽብር አጋሩ ህወሃት አቤት ማለቱ ከዚህ ቀደም በሁለቱ የሽብር ቡድኖች ሲፈጸም የነበረውን ግፍ ለማስቀጠል ካላቸው ፍላጎት የመነጨ ነው ብለዋል።

በሚዛን አማን ዩኒቨርሲቲ የህግ መምህርና ተመራማሪ መሐመድ ሰይድ÷ ሸኔ በአሸባሪው ህወሃት ቡድን የጦር መሳሪያ እና የገንዝብ ድጋፍ እየተደረገለት የቆየ ሌላኛው የጥፋት እጅ መሆኑን አስረድተዋል።

የኦሮሞ ህዝብ ለነጻነቱ እና እኩልነቱ መከራ በሚቀበልበት ጊዜ አንድ ጥይት መተኮሱ ሳይሰማ ዛሬ የኦሮሞ ህዝብ በልጆቹ ደም ነጻነቱን ማስከበር ሲጀምር÷ ሸኔ ከኦሮሞ ህዝብ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር ለሽብር ተግባር መሰናዳቱ ዛሬም ሆነ ትናንት ሁለቱም የሽብር ቡድኖች የኦሮሞ ህዝብ ጠላት መሆናቸወን ያረጋገጠ ነው ብለዋል የፖለቲካ ጉዳዮች ተንታኙ ንጋቱ አበበ።

የሽብር ቡድኖቹ ህዝቡ እያሳየ ባለው አንድነት ተስፋ በመቆረጣቸው የመንግስት ትኩረት ወደተለያየ አቅጣጫ እንዲበታተን ጥረት እያደረጉ ሰለመሆኑ ነው ምሁሩ ያነሱት።

ሸኔ አሁን ላይ ለሃገር ስጋት የሚፈጥር ወታደሮች ባይኖሩትም እየተሽሎከለከ በንጹሃን ላይ የከፋ ጥቃት እንዳይፈጽም መንግስት ችላ ሊለው አይገባም ነው ያሉት ምሁራኑ።

ለዚህም የክልል መንግስታት የፌዴራል መንግስት የማያዳግም እርምጃ ለመወስድ የሚያስችለውን የፖለቲካ ህዝባዊ ንቅናቄ መፍጠር ይጠበቅባቸዋል።

መንግስትም የሸኔ ሽብር ቡድን ትኩረት አድርጎ በሚንቀሳቀስባቸው አካባቢዎች ከህዝቡ ጋር ተቀናጅቶ በመስራት ቡድኑን አፈር የማልበሱን ሂደት ሊያፈጥን ይገባል ብለዋል።

አሸባሪዎቹ ሸኔ እና ህወሃት አድርገነዋል ያሉት ጥምረት ቀድሞውኑ በእቡህ በህዝብ ላይ ሲፈጽሙት የቆየውን የሽብር ተግባር ጋዕድ ያወጣ ነው ሲሉም ምሁራኑ ከጣቢያችን ጋር ባደረጉት ቆይታ ገልጸውልናል።

በላይ ተስፋዬ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version