የሀገር ውስጥ ዜና

የኬንያ አስጎብኚዎች እና የጉዞ ወኪሎች ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው

By Meseret Demissu

August 26, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ የኬንያ አስጎብኚ ድርጅቶች፣ የጉዞ ወኪሎች፣ የሳፋሪ ባለሙያዎች እና ጋዜጠኞች የኢትዮጵያን ታሪካዊ የቱሪስት መዳረሻዎች ይጎበኛሉ።

እነዚህ አስጎበኚዎች እና ጋዜጠኞች የኢትዮጵያን የቱሪስት መስህቦችን በማስተዋወቅ እና ለቱሪስቶች በመሸጥ እንዲሁም የኢትዮጵያ በጎ ገፅታ ለኬንያ እና ለሌሎች የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ያስተዋውቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በፈረንጆቹ ከነሀሴ  28 እስከ 31 ቀን 2021  የሚደረገውን ይህንን ጉብኝት ያዘጋጁት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ቱሪዝም ኢትዮጵያ በጋራ በመተባበር ነው።

በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር መለስ ዓለም በሰጡት ገለፃ፥ የጉብኝቱ ዓላማ እየተጠናከረ የመጣውን የኢትዮጵያ እና ኬንያ የንግድ ትስስርን የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ ነው ማለታቸውን ኬንያ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!