የሀገር ውስጥ ዜና

በክልሉ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ20 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

By Meseret Awoke

August 26, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በ2013 በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ20 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የክልሉ ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ፡፡

ተቋሙ ከተለያዩ የገቢ አርዕስቶች 20 ቢሊየን 560 ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ የያዘውን ዕቅድ ለመፈፀም ጥረት መደረጉን የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ሀላፊ ወይዘሮ ብዙአየሁ ቢያዝን ገልፀዋል።

ቢሮው በበጀት ዓመቱ መጨረሻ 20 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ከግብር ከፋዮች የተሰበሰበ ሲሆን÷ ይህም የዕቅዱን 98 ነጥብ 7 በመቶ መፈፀሙን ያመላክታል ነው ያሉት ኃላፊዋ፡፡

በዚህም ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት አንፃር በ7ነጥብ 2 ቢሊየን (56 በመቶ) ብልጫ አሳይቷል ብለዋል፡፡

በወቅታዊ ሁኔታው የአራት ዞኖች የተጠቃለለ ሪፓርት አልደረሰም ያሉት ኃላፊዋ ለተመዘገበው የተሻለ አፈጻጸም ስራውን በጥብቅ ክትትል መምራት መቻሉ አሳሪ የነበሩ አሰራሮች፣ መመሪያዎች እና አዋጆች የማሻሻል ብሎም የመቀየር ሥራ መሠራቱ ለተመዘገው ውጤት ምክንያቶች ናቸው ተብሏል፡፡

ክልሉ በርካታ ችግሮችን ተቋቁሞ ከህልውናው ጎን ለጎን የገቢ መሰብሰብ ስራውን በተሻለ መንገድ መፈፀሙ በቀጣይ ዓመት የተሻለ ለመፈፀም አቅም ይሆነዋል ተብሏል።

ምናለ አየነው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!