Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አገራዊ የምርምር ስትራቴጂና የትኩረት መስክ ልየታ ሰነድ እየተዘጋጀ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አገራዊ የምርምር ስትራቴጂ እና የትኩረት መስክ ልየታ ሰነድ ማዘጋጀት ተጀመረ፡፡

የሰነዱ ዝግጅት የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ፣የከፍተኛ ትምህርት፣ የቴክኒክና ሙያ እና የምርምር ተቋማት እንዲሁም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችና ሌሎች የሚመለከታቸውን ባለድርሻ አካላት በማሳተፍ ወደ ስራ ተገብቷል፡፡

ሰነዱ ከአገሪቱ የፍኖተ ብልጽግና እቅድ የሚነሳና ለአገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት ቁልፍ ድርሻ አላቸው ተብለው ከተለዩ ግብርና፣ ማይንኒግ፣ ቱሪዝም፣ ማኑፋክቸሪንግ እና ከአይሲቲ በተጨማሪ ጤና፣ ሰላም ልማትና ዲፕሎማሲ እንዲሁም ትምህርት ላይ እንደ አገር የምርምር ስራው የሚመራበትን ስልት በመንደፍ እውቀትና ሃብትን በማቀናጀት የምርምር ስራዎች ድግግሞሽ ለምርምር የሚመደብን በጀት ያለብክነት ለመጠቀም ያስችላል ተብሏል።

ሰነዱ ተዘጋጅቶ ሲጠናቀቅም በሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላትና ምሁራን ተተችቶ በተያዘዉ በጀት ዓመት ወደ ስራ የሚገባ መሆኑን ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version