Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በባህርዳር ከተማ ለህልውና ዘመቻው ህብረተሰቡ የሚያደርገው ተሳትፎ ቀጥሏል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በባህርዳር ከተማ ሀብት በማሰባሰብ እና ስንቅ በማዘጋጀት ለህልውና ዘመቻው ህብረተሰቡ የሚያደርገው ተሳትፎ በተሻለ ሁኔታ መቀጠሉን የከተማው ሀብት አሰባሳቢና ሎጅስቲክ ኮሚቴ አስታወቀ።

የኮሚቴው ዋና ሰብሳቢ አቶ አላዩ መኮነን÷ አሸባሪው የህወሓት ቡድን በአማራ ከልል ላይ ጦርነት መክፈቱን ተከትሎ የባህርዳር ከተማ ህዝባዊ ደጀንነቱን በተግባር በመሳተፍ እያሳየ ነው ብለዋል።

በስድስቱ ክፍለከተሞች በተፈጠረው አደረጃጀት ሴቶች ስንቅ በማዘጋጀት ወጣቱ የከተማዋን ፀጥታ በመጠበቅ ሌላው የህብረተሰብ ክፍልም ገንዘብ በመለገስ እየተሳተፈ ነው።

በእስካሁኑ ሀብት ማሰባሰብ ስራ በከተማ ደረጃ 118 ሚሊየን ብር ገንዘብ መሰብሰቡን አቶ አላዩ ገልፀዋል።

ስንቅ ዝግጅትን በተመለከተ 2ሺህ 161 ኩንታል ምግብ ነክ የሆኑና ያልሆኑ የስንቅ አይነቶች ከህብረተሰቡ ተሰብስቧል፤ ተዘጋጅቷል።

በስንቅ ዝግጅቱ ሲሳተፉ ያገኘናቸው የከተማዋ ነዋሪዎች በሰጠቱት አስተያየት አሸባሪው ቡድን እስኪደመሰስ የጀመሩትን ማንኛውንም አይነት ድጋፍ እንቀጥላለን ብለዋል።

የባህርዳር ከተማ ነዋሪ የተጀመረው የህልውና ዘመቻ በስኬት እስኪጠናቀቅ ድረስ ድጋፉን በተሻለ ወኔ እንዲቀጥል ኮሜቴው አሳስቧል።

በምናለ አየነው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version