የሀገር ውስጥ ዜና

ሽብርተኞቹን ህወሓትንና ሸኔን የሚያወግዝ ሰልፍ በጌዴኦ ዞን ተካሄደ

By Feven Bishaw

August 26, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሽብር ቡድን የሆኑትን ህወሓትንና ሸኔን የሚያወግዝና የሀገር መከላከያ ሰራዊትን የሚደግፍ ሰልፍ በጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ ተካሄደ፡፡

ነዋሪዎቹ በሰልፉ ሀገሪቱን ከጥፋት ሀይሎች ለመታደግና ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የሚያደርጉትን ሁለንተናዊ ድጋፍ ከማድረግ ባለፈ እስከ ህይወት መስዋዕትነት ዋጋ ለመክፈል መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል ።