Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የደሴ ከተማ ነጋዴዎች ለህልውና ዘመቻው ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የደሴ ከተማ አስተዳደር በወቅታዊ ክልላዊና ሀገራዊ ሁኔታዎች ላይ ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር ባካሄደው ውይይት ለህልውና ዘመቻው ከ15 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ተሰብስቧል፡፡

የንግዱ ማኅበረሰብ እያደረገ ያለውን ድጋፍም አጠናክሮ እንዲቀጥል የደሴ ከተማ ንግድ ኢንዱስትሪና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ ዮናስ እንዳለ ጠይቀዋል፡፡

ተሳታፊዎቹም የህወሓት ቡድን በክልሉ ተጨማሪ ጥፋቶችን ሳይፈጽም ለማጥፋት በሚደረገው ዘመቻ ከገንዘብ ድጋፍ በተጨማሪ በግንባር በመሰለፍ የሚጠበቅባቸውን ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

ክልሉን ለማዳከም የሚደረገውን የኢኮኖሚ አሻጥር በመታገል እና አላስፈላጊ የዋጋ ንረት እንዳይኖር ለማድረግ ከመንግሥት ጎን በመሆን እንደሚሠሩ መናገራቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡

የደሴ ከተማ ከንቲባ አበበ ገብረ መስቀል በህወሓት ቡድን ተፈናቅለው በከተማዋ ለተጠለሉ ነዋሪዎች የንግዱ ማኅበረሰብ ላደረገው ድጋፍ አመስግነው÷ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version