Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በደቡብ ወሎ ዞን 116 ሰርጎ ገቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የትህነግ የሽብር ቡድን እንዳሰማራቸው የተጠረጠሩ 116 ሰርጎ ገቦች በቁጥጥር ስር ማዋሉን የደቡብ ወሎ ዞን ገለጸ።
የደቡብ ወሎ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሰይፋ ሰይድ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሉት÷ ዞኑ የትህነግ የሽብር ቡድን ወረራ ከፈጸመበት ሰሜን ወሎ ዞን የሚዋሰን በመሆኑ ዞኑን ከሰርጎ ገቦች ለመጠበቅ ጠንካራ አደረጃጀት ተፈጥሮ እየተሰራ ነው።
በዞኑ በከተማና ገጠር በተፈጠረው አደረጃጀት 2 ነጥብ 7 ሚሊየን የህብረተሰብ ክፍሎች ተደራጅተው አካባቢያቸውን ከሰርጎ ገቦች እየጠበቁ ነው ተብሏል፡፡
በዚህም አመርቂ ውጤት ተመዝግቧል ያሉት አቶ ሰይፉ ሰይድ እስካሁን 116 ሰርጎ ገቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው ነው ሲሉ ገልፀዋል።
የትህነግ ጁንታ በሚያሰማራቸው ሰርጎ ገብና ተላላኪዎች በሀሰት መረጃ ህዝብን የማሸበር ስራ ሲሰራ ቆይቷል ያሉት አቶ ሰይፋ፥ ህብረተሰቡ ለሽብር ቡድኑ የተሳሳተ መረጃ ጆሮ ሊሰጥ እንደማይገባ ተናግረዋል፡፡
የትህነግ ሽብር ቡድን ሀገር ለማፍረስ አቅዶ እየሰራ መሆኑንም በመጥቀስም የቡድኑን እኩይ ሴራ ለመመከትና ለማጥፋት ወጣቱ የመከላከያ ሰራዊትን እንዲቀላቀል፣ ህዝቡም የጀመረውን የደጀንነት አኩሪ ገድል አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።
በግርማ ነሲቡ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version