Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሳልቫ ኪር ማያርዲት ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል።

ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ፣ የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚልና የመከለከያ ሚኒስትር ዶክተር ቀነዓ ያደታን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በኢትዮጵያ ቆይታቸው በሁለትዮሽ ጉዳዮች ከተለያዩ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ጋር እንደሚመክሩ ይጠበቃል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version