Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን አዲስ ያዘጋጀውን የተቋሙን ዓርማና የደንብ ልብስ አስመረቀ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 20 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን አዲስ ያዘጋጀውን የተቋሙን ዓርማ፣ የደንብ ልብስና የማዕረግ ማስተዋወቂያ መርሃ ግብር በዝዋይ ማረሚያ ማዕከል አካሂዷል።
በፕሮግራሙም ላይ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ፣ የፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄነራል ዳመነ ዳሮታ፣ የፌዴራልና የክልል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ኮሚሽነሮች፣ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራሎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በዛሬው ዕለት ይፋ የሚደረገው እና ከተቋሙ ዓላማና ተልዕኮ ጋር አብሮ የሚሄድ የማረሚያ ፖሊስ አባላት ደንብ ልብስ፣ ማዕረግና ሊሻን የጥራት ደረጃውን የጠበቀ፣ በሰራዊቱ መካከል መልካም ግንኙነትና አንድነት በሚፈጥር እና የማረሚያ ፖሊስ አባላትን ክብር በሚያስጠብቅ መልኩ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።
አልባሳቱ በቀጣይ ተቋሙ የሚሰራውን ስራ ከአሁን በፊት ይሰራ ከነበረው በበለጠ ተነሳሽት እና ኃላፊነት ስሜት እንዲሰራ የራሱ የሆነ በጎ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሎ ይታመናል፡፡
በበእምነት ዘላለም
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለ
ማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version