Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አሸባሪው ህወሓት በነፋስ መውጫ ባንኮችን ዘርፏል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የነፋስ መውጫ ቅርንጫፍ ከ 900 ሺህ ብር በላይ ዘርፏል።
የቅርንጫፉ ስራ አስኪያጅ አቶ ብርሀን ምናሴ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት የኤቲ ኤም ማሽን በመስበር ከ 300 ሺህ ብር በላይ እንዲሁም የባንኩ ካዝናን በመስበር ከ 600 ሺህ ብር በላይ በአጠቃላይ ከ 900 ሺህ ብር በላይ መዝረፉን ተናግረዋል።
የባንኩን ንብረቶች በሙሉ ፣ የግለሰብ፣ የብድር ፋይልና ማህተም የሚይዝ ኮንክሪት ካዝናን ጨምሮ በርካታ ፋይሎችን አውድሟልም ነው ያሉት።
አሸባሪው ቡድን የባንኩን ጥበቃም በግፍ መግደሉን በመጥቀስም፥ ቡድኑ በነፋስ መውጫ የሚገኘውን ሌላውን የባንኩን ቅርንጫፍ ፊታውራሪ ገብርዬ ቅርንጫፍን በመዝረፍ ጥበቃውን መግደሉንም ገልጸዋል።
የዳሸን ባንክ ቅርንጫፍንም በመዝረፍ ጥበቃውን በአሰቃቂ ሁኔታ መግደሉን የአይን እማኞች ነግረውናል።
በከተማ የሚገኙ ሌሎች ባንኮችም በቡድኑ ተዘርፈዋል ነወ ያሉት።
በዙፋን ካሳሁን እና በምንይችል አዘዘው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version