Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኢትዮጵያ ኦርቶፔዲክስ እና ትራሞቶሎጂ ማህበር 15ኛ ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኦርቶፔዲክስ እና ትራሞቶሎጂ ማኅበር 15ኛ ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔ እና ሳይንሳዊ ኮንፈረንስ ዛሬ ተካሂዷል፡፡
 
ጉባዔው “በግጭቶች ጊዜ የሚጠፈሩ ጉዳቶችን ማከም” በሚል መሪ ቃል መካሄዱን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡
 
እንደ ትራፊክ አደጋ ፣ ግንባታ ሥራ ፣ ማሽነሪዎች ፣ ግጭቶች የተፈጥሮ አደጋዎች እና በተለያዩ ምክንያቶች የሚደርሱ ጉዳቶች ከመከላከል ጀምሮ ወቅታዊ ሕክምና መስጠት እና ማገገም ድረስ ከፍተኛ ትኩረት የሚሹ ዋና ዋና ተግዳሮቶች መሆናቸውን ሚኒስትሯ ተናግረዋል፡፡
 
በግጭት አካባቢዎች ጉዳት የደረሰባቸውን ለመንከባከብ ካለው ቁርጠኝነት ጨምሮ የአደጋ እና የአጥንት ህክምና እንክብካቤ አገልግሎትን ለማሻሻል እና ሥልጠናን ለማጠናከር ማህበሩና አባላቱ እያደረጉ ላሉት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version