አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሠራተኛና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ በአርባምንጭ ከተማ ለሚያስገነባው የአረጋውያን ማዕከል የመሠረተ ድንጋይ አስቀምጠዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ የጋሞ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ ፣ የአርባምንጭ ከተማ ከንቲባ አቶ ሰብስቤ ቡናቤ እና ሌሎች የፌደራል ፣ የክልል፣ የዞን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና ታዋቂ አርቲስቶች ተገኝተዋል፡፡