Fana: At a Speed of Life!

ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ በአርባምንጭ ከተማ ለሚያስገነባው የአረጋውያን ማዕከል የመሠረተ ድንጋይ ተቀመጠ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሠራተኛና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ በአርባምንጭ ከተማ ለሚያስገነባው የአረጋውያን ማዕከል የመሠረተ ድንጋይ አስቀምጠዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ የጋሞ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ ፣ የአርባምንጭ ከተማ ከንቲባ አቶ ሰብስቤ ቡናቤ እና ሌሎች የፌደራል ፣ የክልል፣ የዞን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና ታዋቂ አርቲስቶች ተገኝተዋል፡፡

ማዕከሉም በ50 ሚሊየን ብር ወጪ እንደሚገነባ ተገልጿል፡፡

የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ መስራችና ስራ አስኪያጅ ሲስተር ዘብደር ማዕከሉ የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር እና የጋሞ ዞን በሰጡት 6 ሺህ ካሬ ላይ እንደሚገነባ መናገራቸውን ከዞኑ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.