የሀገር ውስጥ ዜና

በህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

By Meseret Awoke

August 25, 2021

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢሉባቦር ዞን ቡሬ ወረዳ በህገ ወጥ ጦር መሳሪያ ዝውውር የተጠረጠሩ ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ አስታወቀ።

ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት ዛሬ በሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3- 15074 አ.አ የሆነ ዶልፊን የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ጭነው ሲያጓጉዙ ተደርሶባቸው መሆኑን የቡሬ ወረዳ ፖሊስ ምክትል አዛዥ ምክትል ኢንስፔክተር ጳውሎስ ታመነ ተናግረዋል።

መነሻውን ጋምቤላ ክልል አድርጎ በኢሉባቦር ዞን በኩል ቡሬ ከተማ ፍተሻ ጣቢያ እንደደረሰ ተሽከርካሪው ውስጥ በተደረገው ፍተሻ 12 ክላሽንኮቭ እና አምስት የጥይት መያዣ ካርታ መገኘታቸውን አስታውቀዋል።

የጦር መሣሪያውን እንደጫኑ የተጠረጠሩ አሽከርካሪውና ሌላ ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሚገኝ ምክትል ኢንስፔክተር ጳውሎስ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!