Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በልደታ ክፍለ ከተማ ያስገነባውን የአቅመ ደካማ መኖሪያ ቤት አስረከበ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በልደታ ክፍለ ከተማ ያስገነባውን የአቅመ ደካማ መኖሪያ ቤት በዛሬው እለት አስረክቧል።

መኖሪያ ቤቱ በክፍለ ከተማው ቀበሌ 47 የሚገኝ ሲሆን የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አድማሱ ዳምጠውን ጨምሮ የተቋሙ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ነው ርክክቡ የተደረገው።

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አድማሱ እጅ ለእጅ ተያይዘን ከሰራን የማናሸንፈው ነገር የለም ብለዋል።

ይህን የቤት እድሳትም ምሳሌ ሆነን አከናውነናል ነው ያሉት።

የቤት እድሳቱ የተደረገላቸው ወይዘሮ መሰረት አለማየሁ በበኩላቸው ባማረ ቤት ውስጥ በመግባታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ምስጋና አቅርበዋል።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ከአንድ ወር በፊት የመኖሪያ ቤት እድሳቱን ማስጀመሩ ይታወሳል።

በወቅቱም ቤቱን ለመኖሪያ ምቹ በማድረግ ለማስረከብ እንደሚሰራ መዘገባችን ይታወሳል።

በዳግማዊ ዴክሲሳ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version