Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የመጀመሪያዎቹ የአፍጋኒስታን ተፈናቃዮች ዩጋንዳ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በመጀመሪያው ዙር 51 ከካቡል የተነሱ የአፍጋኒስታን ተፈናቃዮች ዩጋንዳ ገቡ፡፡

እንደ ዩጋንዳ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ÷ ከአፍጋኒስታን በግል ቻርተር አውሮፕላን የተነሱት የመጀመሪያው ተፈናቃዮች ቡድን ኢንቴቤ ዓለም ዓቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ዛሬ ማለዳ ደርሷል።

አፍጋነውያኑ ዩጋንዳ አርፈው ወደ አሜሪካና ወደ ተለያዩ ሀገራት እንደሚሄዱም ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው።

ተፈናቃዮቹ የኮቪድ19 ምርመራ የተደረገላቸው እና እስከ ቀጣይ በረራቸው ድረስ በማቆያ ጣቢያ የሚቆዩ ወንዶች፣ ሴቶች እና ሕፃናት መሆናቸውም ተመላክቷል፡፡

በረራው ታሊባን አፍጋኒስታንን መቆጣጠሩን ተከትሎ በሀገሪቷ በደረሰው ግጭት የተፈናቀሉትን ሰዎች በዩጋንዳ በኩል ለማጓጓዝ የአሜሪካ መንግስት የዩጋንዳን ትብብር መጠየቁን ተከትሎ የተደረገ እንደሆነ ነው የተገለፀው፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት አንድ የመንግስት ባለሥልጣን ዩጋንዳ ከአሜሪካ በቀረበላት ጥያቄ መሰረት ወደ 2ሺህ አፍጋናውያን ስደተኞችን ትቀበላለች ማለታቸውን ቢቢሲ በዘገባው አስታውሷል።

ዛሬ ዩጋንዳ የደረሱት ተፈናቃዮች ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆዩ ግን የታወቀ ነገር የለም፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version