የሀገር ውስጥ ዜና

የጎፋ ዞን ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ከ36 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ

By Tibebu Kebede

August 25, 2021

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጎፋ ዞን በሶስተኛው ዙር በአይነት ድጋፍ 231 ሰንጋዎች እና ተጨማሪ በግና ፍየሎችን ጨምሮ ከ36 ሚሊየን 835 ሺህ ብር በላይ ድጋፍ አድርጓል።

የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶክተር ጌትነት በጋሻው ኢትዮጵያ ረጅም ታሪክ ያላትና ሉዓላዊነቷን ጠብቃ የኖረች ሀገር መሆኗን በመግለጽ ሀገሪቱ አሁን የገጠማትን የውስጥና የውጭ ፈተና በዛሬው ትውልድ ትወጣዋለች ብለዋል።

አሸባሪው ህወሓት እየፈጸመ የሚገኘውን የሽብር ተግባር በማውገዝ የመከላከያ ሠራዊቱን ለማበረታታትና ደጀን ለመሆን የጎፋ ዞን ህዝብ ላሳየው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

የዞኑ ማህበረሰብ ለመከላከያ ሠራዊት ከሚያደርገው ድጋፍ በተጨማሪ ሁለም በተሰማራበት መስክ በትጋት በመስራት የኢትዮጵያን ብልጽግና ማረጋገጥ እንዳለበትም አስገንዝበዋል።

በድጋፍ ሰልፉ ላይ የቀድሞ ሠራዊት አባላት መገኘታቸውን የደቡብ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።

የጎፋ ዞን በመጀመሪያውና በሁለተኛው ዙር ለሀገር መከላከያ ሠራዊት የአይነትና የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉ ይታወሳል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!