Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በፓሪስ አሸባሪው ህወሓትን የሚያወግዝ ሰልፍ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በፈረንሣይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራዊያን ለመከላከያ ሠራዊት ያላቸውን ድጋፍ እና የህወሓት የሽብር ድርጊትን የሚያወግዝ ሰልፍ አካሄዱ፡፡

በሰልፉ አሸባሪው የህወሓት ቡድን በአማራ፣አፋር፣ እና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በሰላማዊ ዜጎች ላይ የጅምላ ግድያ ማድረሱን የሚያወግዙ መልዕክቶች ተስተጋብተዋል፡፡

የህዝቦችን መፈናቀል እና ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እያደረሰ ያለው የሽብር ቡድኑ ከድርጊቱ ሊቆጠብ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

ለዚህም ዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ ትብብር እንዲያደርግ ነው የጠየቁት ፡፡

ምዕራባውያን ሀገራትም በኢትዮጵያ ላይ አላስፈላጊ ጫና ከማድረግ ተቆጥበው ከኢትዮጵያ ጎን ሊቆሙ እንደሚገባ ጥሪ ማስተላለፋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version