Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን አመራርና ሰራተኞች ለመከላከያ ሰራዊት ደም ለገሱ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን አመራርና ሰራተኞች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ደም ለገሱ፡፡
በዚህ ወቅት አመራርና ሰራተኞቹ ደም በመለገሳቸው ደስተኞች እንደሆኑ ገልፀው ÷ይህም “እኛ ለመከላከያ ሰራዊት ማድረግ ከሚገባን በጣም ትንሹ ነገር ነው” ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ከዚህ ጋር አያይዘው ሰራተኞቹ ከዚህም በፊት የ1 ወር ደመወዛቸውን ለሰራዊቱ ማበርከታቸውን ገልጸው÷ ከዚህም በኋላ በተለያየ መልኩ በሚደረገው ድጋፍ ከሀገር መከላካያ ሰራዊት ጎን እንደሚሆኑ መግለፃቸውን ከትራንስፖርት ባለስልጣን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version