የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደር አብዱልፈታህ አብዱላሂ በሶማሊያ ከቱርክ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

By Meseret Awoke

August 25, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 19፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሊያ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር አብዱልፈታህ አብዱላሂ በሶማሊያ ከቱርክ አምባሳደር መህመት ይልማዝ ጋር ተወያይተዋል።

አምባሳደር አብዱልፈታህ ስለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድርድር እና የትግራይ ክልልን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ገለጻ ማድረጋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ትግሉ ከትግራይ ህዝብ ጋር ሳይሆን ሀገርን ለማፍረስ ከሚሰራው የህወሓት ቡድን ጋር መሆኑንም አምባሳደሩ አስረድተዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!